ልኳትን በሰንደቅህ ስር ግርጌ፤
የፅዋ ደምክን ፈልጌ፤
ባክህ አባት ሆይ ስማኝ ደምህ ሕዝብህን አደራ፤
ለሚደርስበት ግርፋት ኢምንት ቁራጯን አልፍራ፤
የሞትም ፅዋ ካለበት ቀድሜ እኔ ልጠራ።
….
አርበኛ አሻግሬ ባዬ ለሜጀር ጀኔራል ከፍያለው ደሴ መታሰቢያ ከጻፈው ግጥም ለቅምሻ የቀረበ …
ለተከበራችሁ የትግሉ ባለቤቶች፤ ደጋፊዎችና አጋሮች በሙሉ፤
የአማራ ፋኖ ድምጽ ፩ ዓመት፣ ፭ እትም፤
▪ በርዕሰ አንቀጿ ጠንካራ ሀገረመንግስት ለመገንባትና የማይናወጥ እውነተኛ ለውጥ ለማምጣት ለብዙ ዘመናት የዘለቀውን የማያባራ ስደት ለማስቆም ሰፊ ጠንካራ የፖለቲካ ማህበረሰብ መመስረትን፣ በዚህ ረገድ አፋሕድም እንደተቋም ትግሉን በኃላፊነት በመምራት ብቻ ሳይሆን ይህንን ታሪካዊ አደራ ለመወጣት እየተጫወተ ያለውን ሚና ትዘረዝራለች። እንዲሁ የአማራን ህዝብ የሚመጥን ንቁና ጠንካራ የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር የገጠመውን ችግርና ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መደረግ ስላለበት መፍትሔ ዘርዝራለች፣
▪ የሜጀር ጄኔራል ከፍያለው ደሴ መታሰቢያ ግጥም፣
▪ አርበኛ እስክንድር ነጋ በፓን አፍሪካኒዝም ላይ ያቀረበውን ጠንካራ ሀሳብና ሀተታን ይዛለች። በዚሁ ሀተታ ላይ አርበኛ እስክንድር ፕሮፌሰር ሉቡምባ ለፓን አፍሪካ መሳካት የሚያደርጉትን ትግል በመጥቀስ እና በማመስገን AfCFTA ለአህጉራዊ ውህደት እንዲተገበር አሳስቧል።
ሙሉ ዕትሟን እንዲያነቡ ተጋብዘዋል።
ተከታተሏት 📖
Voice of Fano Vol. 1 No. 5 features an editorial on Amhara as a political community, a memorial poem for Maj. Gen. Kefyalew Dessie, and Eskinder Nega on Pan-Africanism. The editorial urges forming a broad political community to secure lasting change and end decades of persecution; AFPO leads. Eskinder spotlights Gen-Z-driven digital mobilization, echoing P.L.O. Lumumba, and urges realizing AfCFTA for continental integration.
You’re invited to read!