Volume 1, Number 4 | አንደኛ ዓመት፣ አራተኛ እትም

የአማራ ፋኖ ድምጽ አንደኛ ዓመት፣ አራተኛ እትም (ቁጥር ፬)፣

የድርጅታችን ልሣን “የአማራ ፋኖ ድምጽ”  ፩ኛ ዓመት፣ አራተኛ እትም (ቁጥር ፬) በርዕሰ አንቀጿ ወሳኝ መልዕክት ይዛለች። 

የተዋሃደ፣ የተደራጀ ሕዝብ የጠንካራ ሀገረ መንግሥት መሠረት መሆኑን፣ እንዲሁም ስርዓት አልበኝነትን በመከላከል ሰላምና ዕድገትን ለማስፈን እንደሚያረጋግጥ አፅንዖት ሰጥታለች። 

ከቬትናምና ከቻይና የቀረቡት ምሳሌዎች የፖለቲካ ማህበረሰቦች በትምህርት እና በቅስቀሳ እንዴት እንደተገነቡ፣ ኢትዮጵያ ግን ከከፋፋይ ሥርዓት እና ከፖለቲካ ባህል መዳከም ጋር እየታገለች እንደምትገኝ፤ ይህም አንድነትን አስፈላጊ ማድረጉን ተንትና አቅርባለች። 

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት በአዲስ ዓመት መልእክቱ ለኢትዮጵያውያን በተለይም ለአማራው ህዝብ መልካም ምኞቱን ገልጿል። 

ትግሉ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በደረሰበት በዚህ ወቅት አንድነት፣ መርኅ እና ቁርጠኝነት እንዲኖርም ይጠይቃል። 

ድርጅታችን አፋሕድ በአዲሱ ዓመት አምስት ግቦችን ማስቀመጡ ይታወሳል። 

የአፋሕድ አምስቱ ግቦች አንድነት፣ የስትራቴጂካዊ ድል መሰረት የሆነው ወታደራዊ አስተምህሮን ማሳደግ፣ የፖለቲካ የበላይነት ያለው የትጥቅ ትግል፣ ዲፕሎማሲ እና ፋይናንስን የተመለከቱ ናቸው፡፡ 

እነዚህን ግቦች ለማሳካት የአማራ አንድነት ወሳኝ ግብዓት መሆኑን አፋሕድ ያምናል። ይህንንም በቃል ኪዳን አስሯል። 

የድርጅታችን ልሣን “የአማራ ፋኖ ድምጽ”  ፩ኛ ዓመት፣ አራተኛ እትም (ቁጥር ፬) 
ሙሉ ዕትሟን እንዲያነቡ ተጋብዘዋል።

ተከታተሏት 📖

2018  የተስፋ ዓመት ነው!

ከገፅ 1 እስከ ገፅ 4 ከዚሁ ያለ ሲሆን ገፅ 5ን ከታች ያገኙታል።

In its editorial, the Voice of Fano stresses that a unified, organized population is the foundation of a strong state, preventing anarchy and enabling peace and progress. Examples were drawn from Vietnam and China to show how political communities were built through education and mobilization, while Ethiopia still struggles with division and weak political culture, making unity essential. The New Year’s message from the Amhara Fano People’s Organization extends greetings to Ethiopians, especially the Amhara people, and calls for unity, discipline, and commitment as the struggle enters a decisive phase.

PDF available at: https://thevoiceoffano.com