Volume 1, Number 3 | አንደኛ ዓመት፣ ሶስተኛ እትም

የአማራ ፋኖ ድምጽ አንደኛ ዓመት፣ ሶስተኛ እትም (ቁጥር ፫)

የአማራ ፋኖ ድምጽ በዚህ ሳምንት እትሟ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) “የፋኖ አንድነት የማይናወጥ ቃል ኪዳን” የትግሉ መሠረት መሆኑን በአፅንዖት የገለጸበትን ሀተታ አካታለች።

አፋሕድ የገጠሙትን ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶች የመቋቋም ልምዱን፣ ለአማራ ሕልውና እና ፍትሕ ያለውን የረዥም ጊዜ ራዕይ እና የተለያዩ የፋኖ አደረጃጀቶች በጋራ መርሆዎች እና ዲሞክራሲያዊ እሴቶች በመመራት አንድ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት ታወሳለች። ያለፉትን የአንድነት ተግዳሮቶች ማለትም መለያየትን፣ አሉታዊ የሚዲያ ዘመቻዎችን፣ ግድያዎችን እና አደረጃጀቶችን የማፍረስ ተግዳሮቶችን ጨምሮ በዝርዝር ገልጾ አንድነትን ለጥንካሬ፣ ለሰላም፣ ለሕጋዊነት እና ለውጤታማ ትግል አስፈላጊ መሆኑን ያረጋግጣል።

አፋሕድ በማኒፌስቶው ዙሪያ ያተኮረ ራዕዩ፣ የጋራ ኃላፊነት፣ ግልጽነት እና የዲያስፖራ ተሳትፎ መርሆዎችን በመዘርዘር ለእውነተኛ አንድነት በፍትሕ እና በይቅርታ ላይ ተመሥርቶ የጋራ ግቦችን በመተግበር እና ከፋፋይ አጀንዳዎችን ባለመቀበል አማራዊ መተማመን በአማራዊ አንድነት ላይ በመገንባት መሆኑን አስምሮበታል።

ጋዜጣዋ የፋኖ አንድነት የአማራን ሕዝብ ነፃነት፣ ክብር፣ ፍትሕ እና እኩልነትን ለማስፈን የማይደራደርበት ቃል ኪዳን መሆኑን አፋሕድ ያረጋገጠበትን አንቀጽ አካታለች። ከአማራ ሕዝብ እና ከሕልውና ትግሉ ጋር የተያያዙ ዋና ዋና ዘገባዎችን ዳሳለች።

ከገፅ 1 እስከ ገፅ 4 ከዚሁ ያለ ሲሆን ገፅ 5ን ከታች ያገኙታል።

ተከታተሏት 📖

The Voice of Fano (Volume 1, Number 3)
The Voice of Fano, in its current issue, emphasizes the Amhara Fano People’s Organization’s (AFPO) unwavering commitment to unity as the cornerstone of its struggle. It highlights AFPO’s resilience through internal and external challenges, its long-term vision for Amhara survival and justice, and its efforts to unify diverse Fano groups under shared principles and democratic values. The issue details past challenges to unity, including divisions, negative media campaigns, assassinations, and sabotage, while reaffirming unity as essential for strength, peace, legitimacy, and effective struggle. It outlines its vision centered around its manifesto, principles of collective responsibility, transparency, and diaspora engagement, stressing that true unity requires justice, forgiveness of past wrongs, adherence to shared goals, and rejection of divisive agendas. The newsletter ultimately frames Fano unity as a non-negotiable covenant necessary to safeguard the Amhara people and advance freedom, justice, and equality. It also highlights top news pertinent to the Amhara People and its struggle.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *